Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 22 ደስታ ላለም የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ደስታ ላለም ጌታ መጥቷል፥
ምድር ተቀበይው፥
ልባችሁን አዘጋጁ።
ሰማይና ምድር
ባንድነት ዘምሩ፥
መዝሙር፥ መዝሙር፥ ለሕፃኑ።
፪፡ ደስታ ላለም አዳኝ ነግሷል።
ሰዎች ዘምሩለት፥
ያለም ሜዳ ተራራውም
ደስታውን ይናገር።
ምድርም ትሸበር፥
ምድር፥ ምድርም፥ ትሸበር።
፫፡ ኃጢአት ይጥፋ፥ ኀዘን ይራቅ፥
ምድርም ከሾህ ትረፍ።
በረከቱን ሊያፈስ መጥቷል፥
መርገምንም ሊሽር።
መርገምንም ሊሽር፥
መርገም፥ መርገምንም ሊሽር።
፬፡ ያለም ገዢ፥ ጻድቅ ፈራጅ፥
ሕዝቡን ሊያገለግል፥
የክብሩ ኃይል፥ የጽድቁም ምንጭ፥
ፍቅር ከላይ ወርዷል።
ፍቅር ከላይ ወርዷል፥
ፍቅር፥ ፍቅር ከላይ ወርዷል።