Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 187 ደስ እንዳለን ይገባናል የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ደስ እንዳለን ይገባናል
ባገኘነው ድንቅ ነገር
አምላክ አሁን ይምረናል
ፍርዳችን ሞት የነበር።
ሊምረን ስለ ወደደ
አንድያ ልጁን ሰደደ
ይህም ደስታችን ሆነ።
፪፡ የሰይጣን ባርያ ነበርኩኝ፥
ራሴን ማዳን አልቻልክም።
በኃጢአቴ ታሠርኩኝ፥
ልጠፋ ለዘላለም።
ወደ ሲኦል እሳት ልወርድ፥
በገዛ ሕሊናየ ፍርድ፥
እንደሚገባኝ ሆነ።
፫፡ ተስፋ ስቆርጥም ከጥፋት
መዳኔ ስላልታየኝ።
አምላክ በምሕረቱ ብዛት
በአባት ፍቅር አየኝ።
በኃጢአቴም ታስሬ
ሳለሁ ተሰማኝ ያባቴ
ዘላለማዊ ምሕረት።
፬፡ እንዲህ ብሎ ተናገረ
እራራላቸዋለሁ።
በኃጢአት የጠፉትን
ለልጄ እሰጣለሁ።
በደሙ ከዘላለም ሞት
ሊያድናቸው ሰደድኩት
ሊሆንላቸውም ሕይወት።
፭፡ አባቱ እንደ ፈቀደ
ወልድ ታዘዘ በፍቅሩ።
ከሰውም ሥጋ ተዋሐደ
የሰማይ ክብሩን ትቶ።
ሕግ በኔ እንደ ፈረደ
የኔን ቅጣት ተቀበለ።
እኔን ነጻ አወጣኝ።
፮፡ ከታላቁ ፍርድ እንድድን፥
ሕይወቱን ለወጠልኝ።
የከበረ የየሱስ ደም፥
በመስቀል ፈሰሰልኝ።
ሲሞት አወጣኝ ከፍርዴ፥
ሆነልኝም አማላጌ።
ባባቱም ፊት ቆመልኝ።
፯፡ ከዚህም ዓለም መከራ
ወዳባቱ ዐረገ።
ለጭንቀቴም የሚራራ
መንፈስ ቅዱስን ላከ።
ለንስሓ ይጠራኛል
በውነትም ይመራኛል።
በልቤም አደረልኝ።
፰፡ ለአምላክ ውዳሴ ይሁን
ምስጋናም ለዘላለም።
ረደኤቱን ለኛ በሰጠን
በአምላክ ተስፋ አለን።
በእኛ ሞት ተፈርዶብን
ስንጨነቅ ያለም መድኅን
ፍርዱን አስወገደልን።