Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 170 ሕዝቦች ሁሉ ዘምሩ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ሕዝቦች ሁሉ ዘምሩ፤
ላምላካችን ተቀኙ።
ሕይወት ያላችሁ ሁሉ፥
አምላክን አመስግኑ።
፪፡ በቃሉ የፈጠረው፥
እጅግ መልካም ድንቅም ነው።
ቀድሞ የተናገረው፥
ተፈጸመ በጊዜው።
፫፡ ካምላክ ጋር ላስታረቀን፥
ከጥፋትም ላወጣን፥
እስከ ሞት ላፈቀረን፥
እንዘምር ሁሉ ቀን።
፬፡ ያለም ፍጥረት በመላ፥
ስብሐት ያቅርብ ለጌታ።
ነፍሴም ደግሞ በደስታ፥
ታመስግን፥ ሃሌ ሉያ።