Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 168 ልጆቹን ለማከማቸት የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ልጆቹን ለማከማቸት
ጌታችን ሲመለስ፥
ጥሩ ስንዴውን ለመክተት
በክብሩ ሲገለጥ፥
ያን ጊዜ ያምላክ ልጆች
በክብሩ ይደምቃሉ፤
ያበራሉም እንደ ዕንቈች
በግሩም አክሊሉ።
፪፡ የሱስም የዋጀውን ገንዘብ፥
በደሙም የነፃ
ቅዱስ መንጋውን ለመሰብሰብ
ወደኛ ሲመጣ
ያን ጊዜ . . .።
፫፡ የሱስንም የሚወዱ
ታናናሾች ልጆች፥
ይሆናሉ ጌጥ ለዘውዱ
የየሱስ ወዳጆች።
ያን ጊዜ . . .።