Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 106 መለከት ንፉ በታላቅ ድምፅ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ መለከት ንፉ በታላቅ ድምፅ
የሱስ ይመለሳል፤
ደስ ይበላችሁ ዘምሩም፤
የሱስ ይመለሳል።
ይመለሳል፥ ይመለሳል፥
የሱስ ይመለሳል።
፪፡ ተራሮች ጩሁ ሜዳም አብሮ
የሱስ ይመለሳል፤
ይገለጣል የታረደው በግ፤
የሱስ ይመለሳል።
ይመለሳል . . .።
፫፡ አውጅ ባሕር በታላቅ ቃል
የሱስ ይመለሳል፤
ለባሕር ዳር ይነገራል፤
የሱስ ይመለሳል።
ይመለሳል . . .።
፬፡ ምድር ሲናወጥ ይታወቃል፥
የሱስ ይመለሳል፤
አውሎ ንፋስ ይነግረናል፤
የሱስ ይመለሳል።
ይመለሳል . . .።
፭፡ በሕዝብ መቆጣት ይታወቃል
የሱስ ይመለሳል፤
ሕዝብ ይራወጣል፤
ዕውቀት ይበዛል፤
የሱስ ይመለሳል።
ይመለሳል . . .።