Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 101 አምላኬ ወዳንተ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ አምላኬ ወዳንተ
እቀርባለሁ
ከከባድ ሸክሜ
ዕረፍት እንዳገኝ።
መዝሙሬን ስዘምር፥
አምላኬ ወዳንተ
አምላኬ ወዳንተ
እቀርባለሁ።
፪፡ ደካማ መእመን ነኝ
በዓለም ላይ፥
ፀሓዩ ጨለማ
ዕረፍቴም ሥቃይ
ቢሆንብኝ እንኳ፥
አምላኬ . . .።
፫፡ የሰማይን መንገድ
ግለጥልኝ፥
በታላቅ ምሕረትህ
ወደ ላይ ምራኝ።
ድምፅህን ሰምቼ፥
አምላኬ . . .።
፬፡ በነቃ ሐሳቤ
ላመስግንህ፥
በኀዘኔ ስፍራ
አንተን ልቅረብህ።
ጸሎቴን ለናድረስ፥
አምላኬ . . .።
፭፡ ከዓለም በደስታ
ወደ ሰማይ
ልሂድ በእልልታ
እመኛለሁ።
መዝሙሬን ስዘምር፥
አምላኬ . . .።