መዝሙር 88 ክርስቶስ ተነሣ፥ ጠላትም ድል ሆነ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ክርስቶስ ተነሣ፥ ጠላትም ድል ሆነ
እሰይ የምሥራች።
እንግዲህ አይጠፋም በየሱስ ያመነ
እሰይ የምሥራች።
ታረቀን ጌታችን ምሕረቱን ላከልን
እሰይ የምሥራች።
ጨለማን አጥፍቶ ብርሃኑን አሳየን
እሰይ የምሥራች።
እሰይ የምሥራች እጅግ ደስ ይበለን
በየሱስ ትንሣኤ መዳን ተገኘልን።
፪፡ ዕዳችንም ቀረ ነፃነት አገኘን
እሰይ የምሥራች።
ከመርገም ኩነኔ ኢየሱስ አወጣን
እሰይ የምሥራች
ተስፋችን ምን ኖርዋል ኢየሱስ ባይመጣ?
እሰይ የምሥራች
ሞት ነበር ገዣችን ኃይለኛ ባላንጣ
እሰይ የምሥራች።
እሰይ . . .።
፫፡ የታለ ሥልጣኑ? ዲያብሎስ ተወጋ
እሰይ የምሥራች።
ጌታችን አወጣን ከጠላት መንጋጋ
እሰይ የምሥራች።
ዲያብሎስ አፈረ ያ ጠላት ተረታ
እሰይ የምሥራች።
ኢየሱስ ይመስገን የሆነን አለኝታ።
እሰይ የምሥራች።
እሰይ . . .።