መዝሙር 85 ነፍሴ ሆይ አሁን ደስ ይበልሽ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ነፍሴ ሆይ አሁን ደስ ይበልሽ
ኦ ልቤ ሐሴት አድርጊ።
በደሙ የሱስ እንደ ገዛሽ
ወንጌል የሚለውን አትርሺ።
አምላክሽም እንደ ወደደሽ
ሰው ሆኖ አንችን እንደ ዋጀሽ።
በከንቱም ጸጋውን እንደ ሰጠሸ
ይህንን ከቶ አትርሺ።
፪፡ በልቤ ጭንቅ ብቻ ቢሰማኝ
እንዳለሁ የሱስ ገዝቶኛል።
ማንኛውም ነገር ቢያስፈራኝ
የደሙ ቤዛ በቅቶአል።
ድሀ ብሆን ብከብርም
ባዝንም ወይም ደስታ ባገኝም።
በሕይወት ብኖርም ብሞትም
የየሱስ ክርስቶስ ገንዘብ ነኝ።
፫፡ በየሱስ ክርስቶስ የሚያምን
ከሌላው ሁሉ ታደለ።
በየሱስ ክርስቶስ ደም ሰላምን
ከአምላኩ ተቀበለ።
አምላክ በፍቀር ያየዋል፤
በሕይወት መንገድ ይመራዋል፤
ወደ ብፅዕና ያደርሰዋል፤
ለዚህም የሱስ ገዝቶታል።