መዝሙር 64 አልረሳውም ያንን ጊዜ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አልረሳውም ያንን ጊዜ
በጌቴሴማኒ
በጣርህ ደም ሲያልብህ
ስለኔ አምላኬ።
አልረሳውም አልረሳውም
ከቶ አልረሳውም
የብርቱ ጣርህን ጊዜ
በጌቴሴማኒ።
፪፡ በዚያ በአትክልቱ ስፍራ
በልቤ አየሁህ።
ቤዛ ሆነህ የኔን ቅጣት
እንደ ተቀበልህ።
አልረሳውም . . .።
፫፡ የደረሰብህ መከራ
አይመዘንም ባሳብ
ወዳጆችህ ሁሉ ካዱህ
አልራራልህም አብ።
አልረሳውም . . .።
፬፡ ፍቅሬ ቢበርድብኝ ላንተ
ክቡር መድኃኒቴ
ሕማማትህን አሳስበኝ
አሳየኝ ቍስልህን።
አልረሳውም . . .።
፭፡ ስለኔ ነው፥ ስለኔ ነው
ደምህ የፈሰሰው
አንተን እንዳመሰግንህ።
አፌን ክፈትልኝ።
አልረሳውም . . .።