መዝሙር 556 አምላክ በታላቅ ጸጋው የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አምላክ በታላቅ ጸጋው
የሰውን ወገን ሁሉ ጠራ
ያለ አድልዎም ለሰው
በማይወሰን ምሕረት ራራ።
በጸጋው ሲያድናቸው
ያዳም ልጆች እኩል ናቸው።
፪፡ ሁሉ ግፍ አደረጉ
ሁሉም ኃጢአትን ሠሩ
አምላክን አልፈለጉም
ጽድቅን ሳያገኙ ቀሩ።
ምኞትም በባሕሪያቸው
አንድ ሳይቀር አሸነፋቸው።
፫፡ ሁሉም እንደ ወደቁ
ሁሉም ኃጥአን እንደ ሆኑ
ሁሉም ደግሞ ጸደቁ
ሁሉም ባምላክ ጸጋ ዳኑ።
በጸጋው ብቻ ጽድቅ ሲሰጥ
ያመነ ያገኛል በርግጥ።
፬፡ በግዞት ቤት ታስሮ
ቅጣት የተፈረደበት
መጽሐፍም ተምሮ
እውቀቱ የታወቀለት
በእነርሱ ሳይኖር ልዩነት
ይድናሉ ባምላክ ምሕረት።
፭፡ ጽድቅ የፈለጉት ሁሉ
ፍጹም ላምላክ የተሰጡ
ኃጥአን የተዋረዱ
ቢመጡ ወደ መስቀሉ
ልዩነት ሳይኖር በሁሉ
ባምላክ ጸጋ ይድናሉ።
፮፡ በበደሉ አዝኖ
በሥራውም የሚያፍር
በኃጢአቱ ጸንቶ
ጸጋን ማመን የማይደፍር
ራሱን ሊያጸድቅ ቢሞክር
ከንቱ ነው የልቡ ምክር።
፯፡ በሰው ጽድቅና ልፋት
የአምላክ ጸጋ አይገኝም።
የሰው ሁሉ ትሩፋት
ፍጹም ሊረዳ አይችልም።
ሰው በሙሉ ኃይል ቢተጋም
ነፍሱን ለማዳን አይበቃም።
፰፡ የሱስ ግን በመስቀሉ
ለኛ ጸጋን አዘጋጀ።
ሞትን በመቀበሉ
ሕይወት ለነፍሳችን ዋጀ
ወደ እርሱ የሚመጣ
ይድናል ከአምላክ ቁጣ።
፱፡ በምሥራቹ ያመነ
በመድኃኒቱ ይድናል።
ሙሉ ተስፋ አለነ
መጽሐፍ እንዲህ ይለናል
ወልድ ያለው ሕይወትም አለው
ሕይወት የለውም ወልድ የሌለው።