መዝሙር 554 በአምላክ ዙፋን ፊት የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ በአምላክ ዙፋን ፊት ድነው የቆሙት
ነጭ ልብስ ለብሰው ለመድኃኒታቸው
ምስጋና የሚሰጡት፥
እኒያ ማን ናቸው?
እነዚያ ዳኑ በየሱስ
ክርስቶስ ደም፤
ነጹም በበጉ ደም።
፪፡ እኒያ ከታላቅ ጭንቀት መጥተው
በበጉ ደም ልብሳቸውን አጥበው፥
የሱስን ተቀብለው፥
የዳኑቱ ናቸው።
እነዚያ ዳኑ . . .።
፫፡ ለዘላለም ድነው ከዚያ ምድር ጣር
በበገና በመሰንቆም አውታር፥
በማይሻር አዲስ መዝሙር፥
ደስታን ያሰማሉ።
እነዚያ ዳኑ . . .።