መዝሙር 532 ኃጢአቴን ምን ያጥበዋል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ኃጢአቴን ምን ያጥበዋል?
የክርስቶስ ደም ብቻ ነው።
ምን ንጹሕ ያደርገኛል?
የክርስቶስ ደም ብቻ ነው።
ኦ ፍጹም ብሩክ ምንጭ
ኃጢአቴን ያጠበው፣
ሌላ ምንጭ አላውቅም
የክርስቶስ ደም ብቻ ነው።
፪፡ እኔን ንጹሕ የሚያደርግ
የክርስቶስ ደም ብቻ ነው።
ይቅርታን የሚሰጠኝ፥
የክርስቶስ ደም ብቻ ነው።
ኦ ፍጹም . . .።
፫፡ ከኃጢአቴ የሚያነጻኝ
የክርስቶስ ደም ብቻ ነው።
የሕይወትም መድኃኒት፥
የክርስቶስ ደም ብቻ ነው።
ኦ ፍጹም . . .።