መዝሙር 531 ሂድ ወደ ጌቴተሴማኒ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሂድ ወደ ጌቴሴማኒ
ፈተናን ፈሪ ሰው ሆይ፥
ላንዲት መራራ ሰዓት
ያዳኝህን ሥቃይ እይ።
ከኀዘኑም ሳትርቅ፥
ከርሱ ጸሎትን ተማር።
፪፡ ወደ ፍርድ ሸንጎ ሄደህ
ጌታን ሲከሰስ እየው፥
ታላቁን የሞት ጽዋ
የሱስ ክርስቶስ የጠጣው።
ላንተ ሲል ነው ወንድሜ፥
መስቀሉን ተካፈለው።
፫፡ በቀራንዮ ተራራ
ሄጄ በግሩ ሥር ልውደቅ።
ድንቁን ታምር አልረሳም፥
ያምላክን ቅዱስ መሥዋዕት።
ተፈጸመ ሲል ልስማው
ሞትንም ከርሱ ልማር።