መዝሙር 480 ጉበኛው ሆይ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ጉበኛው ሆይ፥ በምን ጊዜ
ላይ ደረስን ይሆን?
ፀሐይ መቼ ትወጣለች የአርያም ብርሃን?
ጨለማ አልፎ ጎህ ቀዶአል ሊነጋልን ነው
አትፍራ መድኀናችን
ሕዝቡን ሊያድን ነው።
፪፡ ጉበኛው ሆይ፥ ድንበርዋ ላይ
ደርስን ይሆን ወይ?
የምንናፍቃት ጽዮንን
ታያታለህ ወይ?
ጨለማ ጊዜ አልፎ ድንበርዋ ላይ ነን፥
ከባርነት ያወጣን መድኀን ከኛ ጋር ነው።
፫፡ ጉበኛው ሆይ፥ ንገረን
ወዴት ደርሰናል?
ደርሰናል ወይ ልንሻገር
የልቅሶውን ወንዝ?
አትፍራ ከንዓን ደርሰናል እንዳትሰለች፥
ከቅዱሳን ጋር ወደ ብፅዕና ቀርበናል።
፬፡ ተነሣ ዓይንህን ግለጥ
ነግትዋል ሌሊቱ
የደስታ መለከት ስማ
ደርስዋል መምጣቱ፤
ከየሱስ ጋር ደስ ይበልህ ዘውድን ተቀዳጅ
በረከትህን ተቀበል ከመድኀንህ እጅ።