መዝሙር 460 እንዴት በፈጠነ አኳኋን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እንዴት በፈጠነ አኳኋን
እኒህ ሰዎች ይጓዛሉ
በየዕለቱ በመሰብሰብ
በረከት ይቀበላሉ፤
አድምጣቸው ይነግሩሃል፥
ኢየሱስ ናዝራዊው
መጥቶአል።
ኢየሱስ ናዝራዊው
መጥቶአል።
፪፡ ኢየሱስ የተባለው ማን ነው?
ብዙ ሕዝብ የሚከተለው።
መንገድ አላፊ ሰው ቢሆን፥
እንዲህ በቀናው ነበር ወይ?
አድምጣቸው ይነግሩሃል
ኢየሱስ ናዝራዊው መጥቶአል።
አድምጣቸው ይነግሩሃል
ኢየሱስ ናዝራዊው መጥቶአል።
፫፡ ኢየሱስ ከሰማይ ወረደ
ለተቸገሩ ኃጥአን
እርሱን ለሚቀበል ሁሉ
እኩል ሕይወትን ይሰጣል፤
ዕውር እንዲያይ እንዲሰማም፥
ኢየሱስ ናዝራዊው መጥቶአል።
ዕውር እንዲያይ እንዲሰማም፥
ኢየሱስ ናዝራዊው መጥቶአል።
፬፡ ወደኛ ደግሞ መጥቶአል
የምሥራቹን ሰምተናል
ለኛም ጸጋው ተሰጥቶናል
ልባችንን ይፈልጋል፥
ተቀበሉት በዕልልታ፥
ኢየሱስ ናዝራዊው መጥቶአል።
ተቀበሉት በዕልልታ፥
ኢየሱስ ናዝራዊው መጥቶአል።