መዝሙር 451 ኢየሱስ ክርስቶስ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ኢየሱስ ክርስቶስ
ወዳለም መጥቶአል፤
ኃጢአተኞችን ለማዳን፥
እርሱንም ማመንና መቀበል
ሕይወትና ጽድቅ ይሆነናል።
፪፡ በመላ ዓለም ወንጌል ይሰፋል
መስፋቱን ማን ይከለክላል?
ቅዱስ ቃሉን ሰምተው ሲቀበሉ፥
አሕዛብ በእምነት ይድናሉ።
፫፡ በየሱስ ኃይል ዕውራን ያያሉ
የዲዳ አፍም ይናገራል፤
ሽባዎች አንካሶች ይድናሉ፥
ሙታንም ደግሞ ይነሣሉ።
፬፡ በዚህ የወደቀውን ደረቅ አጥንት
ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ተመልከተው፤
አሁን ሥጋና ጅማት አልብሰህ፥
የሕይወትን እስትንፋስ ስጠው።
፭፡ በእግርህ ታች አሕዛብ ይስገዱ
ለክብርህ ያቅርቡ ምስጋና፤
ከጸጋ ምንጭ ሕይወትን ይውሰዱ፥
ስምህ የቀደስ ሃሌ ሉያ።