መዝሙር 445 አክሊሌን አክብሬ ልጠብቀው ልጠብቀው የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አክሊሌን አክብሬ ልጠብቀው
የሰው ልጅ ጠላት ሰይጣን እንዳይወስደው።
መፈታተኑን አላቋረጠም፥
አንተ እስክትመጣ በክብር ወደዚች ዓለም።
ከባሕር ሞገድ ካየር ነጐድጓድ፥
በሚበልጥ ኃይልህ የሱስ
የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ።
አጥበኸኝ እኔን ድኛለሁ ጌታ፥
ላክሊልህ አብቃኝ የሱስ
እንዳልረታ።
፪፡ እህታህ በዛ መቃተትህ
የኔን የዓለምን ኃጢአት ተሸክመህ።
በጆችህ ሥራ ተጎሳቆልህ፥
እንዲያ ያነባህ ጌታ ምን በበደልህ።
ከባሕር ሞገድ . . .።
፫፡ ጠብቀኝና አክሊሌን ይዘህ
መርከብ ውስጥ ልግባ እኔም
እንደኖኅ ዘመን።
ጎልማሳነቴ ሩጫዬ በቃኝ፥
አክሊሌን ካንተ ልወስድ እጠብቃለሁኝ።
ከባሕር ሞገድ . . .።
፬፡ እንዲያው ብያለሁ ይመስገን ጌታ
ትዝ እያለችኝ ጣርህ በዚያች ጐልጐታ።
ስምህን በእምነት ተቀብያሁ
አክሊሌን ካንተ ልወስድ እጠብቃለሁ።
ከባሕር ሞገድ . . .።
፭፡ ቃል ገብተህልኝ አንዳባትህ
በስሜ እመንና ትድናለህ።
ብለሃልና አማልደኝ ጌታ፥
ላክሊልህ አብቃን የሱስ እንዳልረታ።
ከባሕር ሞገድ . . .።