መዝሙር 442 ስሙ ኢየሱስ ነው አዳኙ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ስሙ ኢየሱስ ነው አዳኙ
ዘላለማዊ ንጉሥ፤
የማይለወጥ ድንቅ ነው ስሙ፥
ታላቅ ነው በእርሱ እመኑ።
ሁላችንንም ይጠራል፥
ሁልጊዜ አይለየንም።
ነፍሴን ከሞት አድኖአታል፥
ወደርሱም ይወስዳታል።
ስሙ ኢየሱስ ነው አዳኙ
ነፍሴን ይቀሰቅሳል፤
በዚህ ስም ነው መዳን ያገኘሁ፥
ሌላ መዳኛ የለኝም።
፪፡ ለኢየሱስ ስም ጣፋጭ ዜማ
በዓለም ሁሉ ዘምሩ፤
ተስፋ ረድኤት ነው ለሁሉ፥
ሰላም ይገኛል ከርሱ።
የጠላት ኃይል ጭንቅም ሁሉ፥
ይሸነፋል በስሙ።
በዚህ ስሙ የጽድቅ መንግሥት፥
ጽኑ ሆኖ ይኖራል።
ስሙ ኢየሱስ . . .።
፫፡ ሌሊት ቢከብድ ቢጨልምም
የኢየሱስ ስም ግን ያበራል፤
የጠፋውን ይመራል፥
ወደቡን ያሳየዋል።
ፀሐይ ብርሃንዋ ሲጠፋ፥
ስሙ ጸንቶ ያበራል፤
ሕዝቡም በሰላም በደስታ፥
ያቀርባሉ ምስጋና።
ስሙ ኢየሱስ . . .።