መዝሙር 424 አንድ ቀን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አንድ ቀን በቅዱስ አምላክ ፊት
ከሰው ነገዶች ሁሉ፥
ሊቈጠሩ የማይቻሉ፥
ጻድቃን ይቆማሉ።
፪፡ አንድ ቀን ያምላክ አገልጋዮች
በመከሩ ወራት፥
ያያሉ ከተማሩቱ፥
የእለፍ አእላፋት።
፫፡ ሊሰጠን በሰማይ ጸዳል
ሰላምም ብፅዕናም፤
ምንኛ ደስታ ይሆናል፥
ምንኛ ምስጋናም።
፬፡ አምላክ ሆይ፥ ጸጋህ ብዙ ነው
ወዳንተ አቅርበን፥
ከጻድቃን ጋር እንድንገኝ፥
በዚያ ታላቅ ቀን።