መዝሙር 412 መልእክት አለኝ ከጌታ ሃሌ ሉያ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ መልእክት አለኝ ከጌታ ሃሌ ሉያ
ላንተ የሚሆን ወዳጄ ሆይ፤
ተጽፎአል በወንጌሉ ሃሌ ሉያ፥
በርሱ ካመንክ እንደምትድን።
እመነው ወዳጄ ሆይ፥
የሱስን ብቻ እመን።
ተጽፎአል በወንጌሉ ሃሌ ሉያ፥
በርሱ ካመንክ እንደምትድን።
፪፡ ፍቅር የሞላው መልእክት ሃሌ ሉያ
ላንተ የሚሆን ወዳጄ ሆይ፤
ከላይ የተላከ ነው ሃሌ ሉያ።
በእምነት ብቻ ተቀበለው።
እመነው ወዳጄ . . .።
፫፡ ልንገርህ አመጣጤን ሃሌ ሉያ
ወደርሱ ወደ አምላኬ፤
በስሙ አምኜ ዳንኩ ሃሌ ሉያ፥
አንተም እመነው ወንድሜ ሆይ።
እመነው ወዳጄ . . .።