መዝሙር 382 የዘላለም ሕይወቴ ነህ መጠጊያና አምባዬ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የዘላለም ሕይወቴ ነህ መጠጊያና አምባዬ
እስከ ፍጻሜ እሄዳለሁ አንተን ተከትዬ።
መንገዴን ሁሉ ካንተ ጋር እስከ መጨረሻ
እከተልሃለሁ የሕይወቴ ጋሻ።
መንገዴን ሁሉ ጌታ ካንተ ጋር
እስከ መጨረሻው ልጓዝ ጌታ ካንተ ጋር።
፪፡ በመከራና በስደት በሚያስፈራ ነገር
ባንተ ጸንቼ እቆማለሁ በሕይወት እንድኖር
የልብን ሰላምንና ደስታን ለሰጠኸኝ
ላንተ ጸንቼ እንድቆም አደራ አስበኝ።
መንገዴን ሁሉ . . .።
፫፡ የሚያሰናክለኝ የለም ከክንፍህ ሥር ነጥቆ
ማንም ሊወስደኝ አይችልም ከእጅህ ፈልቅቆ።
ጠላት ከአንተ ሊነጥለኝ ተግቶ ቢሞክርም
ካንተ ፍቅር በፍጹም ሊለየኝ አይችልም።
መንገዴን ሁሉ . . .።