መዝሙር 37 ቅዱስ ሌት የሰላም ሌት የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ቅዱስ ሌት የሰላም ሌት
ደስታ የሞላበት
በሕፃኑ በእናቱም ዙሪያ
የሚያንጸባርቅ ብርሃን በራ።
በሰማያዊ ሰላም
በሰማያዊ ሰላም።
፪፡ ቅዱስ ሌት የሰላም ሌት
እረኞች ድንቅ አዩ
ያምላክ ክብር ከላይ ተገለጸ
መልአክ ምሥራቹን አበሠረ።
ሲል መድኅን ተወልዶአል
ክርስቶስ የሱስ ተወልዶአል
፫፡ ቅዱስ ሌት የሰላም ሌት
በፍቅሩ መጣልን
የሕፃኑ ፀዳል አበራ
ለሰው የመዳን ጸጋ መጣ።
በጌታ ኢየሱስ ልደት
በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት።