መዝሙር 355 ቃሉን ለመስማት የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ቃሉን ለመስማት
አምላኬን ስቀርበው ይግለጥልኝ።
የጨለማውን ኃይል ከኔ ያርቅልኝ፤
ሕያው ቃሉ ልቤን ያብራልኝ።
፪፡ በቅዱስ መንፈሱ ዛሬ
ይጠራል በትሕትና።
አሁንም በንቃት አድምጠው ቃሉን፤
ለመቀበል ክፈት ልብህን።
፫፡ ግሩም የሆነ ተስፋ ይሰጣል
ዛሬ ለልጆቹ።
ያለ አንዳች ዋጋ ይሰጣል ጽድቁን
አድልዎ ሳያደርግ ለሁላችን።
፬፡ የኃጢአት ቀንበር ከብዶን
ስንኖር አሳረፈን።
ከኃጢአት ባርነት ነፃ አወጣን
በታላቅ ፍቅሩ አድኖናል።