መዝሙር 336 የኢየሱስ ስም ያስደስታል ለሚያምንበት ሁሉ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የኢየሱስ ስም ያስደስታል ለሚያምንበት ሁሉ
በጭንቀቱ ያጽናናዋል ቍስሉን ይፈውሳል።
፪፡ የመንፈስ ቍስል የሚያድን የታወከ ልብም
ለተራበች ነፍስ መና ነው ለደከሙት ዕረፍት።
፫፡ ይህ ድንቅ ስም መሠረቴ ነው ጋሻ መሸሻዬም
ከቶ የማያቋርጥ ምንጭ፥ በማይነገር ጸጋ።
፬፡ የሱስ እረኛ ወዳጄ፥ ነቢይ፥ ካህን ንጉሥ
ጌታ፥ ሕይወት፥ መንገዴ ነህ ተቀበል ምስጋና።
፭፡ የኔ ትጋት ደካማ ነው፥ አሳቤም በራድ
ግን አንድ ቀን በፊትህ ስቀርብ ላመሰግንህ ነው።
፮፡ እስከዚያም ፍቅርህን ላውጅ፥ ባለኝ ትንፋሽ ሁሉ፥
የቡሩክ ስምህም ውዳሴ፥ ከሞት ነፍሴን ያድን።