መዝሙር 332 ኀዘን ወይም ደስታ የሚደርሰን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ኀዘን ወይም ደስታ የሚደርሰን
ማን ያውቃል?
ጌታ የሱስ ከእኛ ጋራ ከሆነ
ይበቃናል።
በርኅሩኅ ድምፁ ያርፋል ነፍሳችን
ሰላምና ደስታ በሕይወት አለን።
፪፡ ችግራችን ሁሉ ባንተ ስናምን
ይወገዳል፤
ኃይል በድካም ረድኤት በመከራ
ይሆነናል።
ጭንቀት የሞላው ይህ ምድራዊ ሕይወት
ከአንተ ዘንድ ይሆነናል ገነት።
፫፡ በምድር ላይ ኃጢአት ስለ በዛ
ይጨልማል
አንተን ስለ ከዳን ፍትህም ከእኛ ይሰወራል
በምሕረትህ እንማጠናለን
በርኅሩህ እቅፍህ ውስጥ አሳርፈን።
፬፡ ቸሩ የሱስ ሆይ በሕይወት በሞት
ረጃችን ሁን
ደግፈነ ከክፋት ስንጋጠም
ስጠን ድሉን።
ሁን ከኛ ጋር ቀናችን ሲመሽብን
ብርሃን ሁንልን ደስታንም ስጠን።