መዝሙር 33 የልደት ማታ እንዴት ያበራል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የልደት ማታ እንዴት ያበራል
መብራት ሲለኮስ በልብ በቤትም።
የመላእክት መዝሙር አሁን ይሰማል
ከጥንቱ ጀምሮ ይዘመራል።
ለአምላክ ይሁን ምስጋና በምድርም ሰላም
ለሰው በጎ ፈቃድ ይሁን ሲሉ ዘመሩ።
የልደት ማታ እንዴት ያበራል
መብራት ሲለኮስ በልብ በቤትም።
፪፡ አምላክ ለምድር የሰጠው ስጦታ
ለኃጢአተኞች መድኅን ሆኖአል።
ፀሐይ በዓለም ላይ እንደሚወጣ
የሱስ ብርሃን ሆኖ መጥቶአል።
በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃንን አየ
በሞት ጥላ ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።
አምላክ ለምድር የሰጠው ስጦታ
ለኃጢአተኞች መድኅን ሆኖአል።
፫፡ በየሱስ ክርስቶስ ነው የተሰጠ
ዕርቅና ጽድቅ ሕይወትና ሰላም።
መድኃኒታችን የወይን ዛፍ ሆነ
የሕይወት ፍሬ ከርሱ ተገኘ።
አንድ ወንድ ልጅ ተሰጠነ ሕፃን ተወልዶዋል
አለቅነቱም በጫንቃው ላይ ይሆናል።
በየሱስ ክርስቶስ ነው የተሰጠ
ዕርቅና ጽድቅ ሕይወትና ሰላም።