መዝሙር 29 ኦ ቅዱስ ሌት ከዋክብት ያበራሉ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ኦ ቅዱስ ሌት ከዋክብት ያበራሉ
ያዳኛችን ልደት ስለሆነ።
ዓለም በኃጢአት ውስጥ ስትጨማለቅ
መጣላት ተስፋዋን ስትጠብቅ
ግሩም ተስፋው ነፍሳችንን ያረካል
ደስ ይበለን ንጋት ሆኖልናል።
ሰገዱለት የመላእኩን ድምጽ ሰሙ
በቅዱስ ሌት በክርስቶስ ልደት
ቅዱስ መዝሙር ለርሱ አቅርቡለት።
፪፡ በእምነት ኃይል በብርሃኑ ተመርተን
በደስታ ልብ እንይ ያንን ሕፃን።
የኮከቡን ብርሃን አይተው ሲሮጡ
ጥበበኞች ከሩቅ ሀገር መጡ
ሕፃኑ ንጉሥ በበረት ተኝቶአል።
በችግርም ወንድማችን ሆኗል።
የኛን ሐሳብ ድካማችንን ሁሉ
እርሱ ያውቃል ወድቀን እንስገድለት
የኛ ንጉሥ ተወለዷል በበረት።
፫፡ ነግሮናል አንዱ አንዱን እንዲወደው
ሕጉ ፍቅር ወንጌሉም ሰላም ነው
ነፃ ወጥቷል ፍጡር ወንድማችን ነው
በርሱ ስም ጭቆና ሁሉ ጠፍቷል።
ስለዚህ ኑ በደስታ እንዘምር
ቅዱስ ስሙም በውስጣችን ይክበር
ክርስቶስ ጌታን አክብረው ለዘላለም
ሥልጣኑን አስታወቅ ለዚች ዓለም
ኃይሉን ስሙን አውጅ ለዘላለም።