መዝሙር 267 ቸር መድኅኔ ሆይ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ቸር መድኅኔ ሆይ፥
እንዴት የሚገርም ነው!
በደምህ መድኃኒት ተገኝቶልኛል፥
ከፍርድ ከቅጣት ነጻ አደረግኸኝ
በቅዱስ ቁስልህም ከሞት አዳንኸኝ።
ታላቅ ነው ፍቅሩ
እሙን ነው ምክሩ።
ለእርሱ ዘምሩ፥
ይስፋ ክብሩ።
፪፡ እንዴት ግሩም ነው
የሱስ ሞተህልኛል!
በቸርነትህ ተቀብለኸኛል፤
ነጻ አወጣኸኝ ከሰይጣን ሥልጣን፤
ድኜ ልመላለስ በፊትህ ብርሃን።
ታላቅ ነው . . .።
፫፡ መድኅኔ ሆይ
ደምህ እንዴት ክቡር ነው፤
ለቍስሌ ሁሉ መድኃኒቴ ነው፤
ሥቃዬን ሁሉ ይፈውሰዋል፤
በኀዘኔም ሁሉ ያጽናናኛል።
ታላቅ ነው . . .።
፬፡ ጌታዬ አምላኬ ሆይ ንጉሤ ነህ፤
ስለ ተሰቀልህልኝ ላመስግንህ፤
ሥጋዬ ሲቀበር በተስፋ ልረፍ፤
የማዳንህን ኃይል በመመልከት ልትረፍ።
ታላቅ ነው . . .።