መዝሙር 230 አምላኬ ምን ይሰጠኛል? የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
(አንዱ ቡድን ሲጠይቅ ሁለተኛው ቡድን መልሱን ይዘምራል)
፩፡ አምላኬ ምን ይሰጠኛል?
– ይቅርታውን ይቅርታውን።
የኔ ልብ ገና ደንዝዞአል
– በርሱ እመን በርሱ እመን።
ረድኤቴ ከየት ይመጣል
– በደሙ ከገዛህ ጌታ።
፪፡ ኃጢአቴ ይሰማኛል
– አትፍራ ተሰቅሎልሃል።
ማነው ነጻ የሚያወጣኝ
– የሞተልህ የሞተልህ።
እንዴት ሰላም አገኛለሁ
– በቁስሉ ውሰጥ በችንካሩ።
፫፡ ዓለም ታስጨንቀኛለች
– አይዞህ ቤቱን ከፍቶልሃል
እረፍትም ትነሣኛለች
– የሱስ በእቅፉ ይይዝሃል።
ደስታውን ልቤ ይናፍቃል
– እመን ብቻ ይሰጥሃል።
፬፡ በጸጋው ያረካኛል ወይ?
– አትረፍርፎ ይሰጥሃል።
ለምን ቃሉ ይወቅሰኛል።
– እንዳትጠፋ ፈልጐሃል።
ይገስጸኛል በምክሩ?
– በፍቅሩ ይታደግሃል።