መዝሙር 185 ድምፅህን እሰማለሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ድምፅህን እሰማለሁ
ወዳንተ ሲጠራኝ
በክቡር ደምህ ለመንጻት
ለኔ በፈሰሰው
መጣሁኝ ጌታ
ወዳንተ መጣሁ።
አንጻኝ በክቡር ደምህ
ለኔ በፈሰሰው።
፪፡ ኃጢአተኛም ብሆን
ብርታት ይሰጠኛል።
በደሙ ኃጢአቴን ያጥባል
ነጻም ያወጣኛል።
መጣሁኝ . . .።
፫፡ ኢየሱስ ይጠራኛል
ፍጹም በሆነ ፍቅር።
ለፍጹም ያንድነት ሕይወት
በሰማይ በምድር።
መጣሁኝ . . .።
፬፡ ይቅር ባይ አምላክ ሆይ
ያዳንኸኝ በጸጋ።
ደስታ ብርታትን የምትሰጥ
በታላቅ ምሕረትህ።
መጣሁኝ . . .።