መዝሙር 18 ከአብ የተላከልን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ከአብ የተላከልን
መድኃኒት አገኘን፥
የሱስ እኛን ለማዳን፥
ወዳለም መጣልን።
በጨለማ ለኖርን፥
በመከራ በሞትም፥
ጌታ ብርሃን ሆነን።
፪፡ እርሱ ሰው ሆኖ መጣ፥
የንጋት ኮከብም
ለአዳም ልጆች ወጣ፤
ተስፋ ብርሃን ሰላም።
የሞት ሥልጣን ተሻረ፥
ከኃጢአት ጋር ቀረ፤
ሰማይ ተከፈተ።
፫፡ የሱስ ክርስቶስ ማረነ፥
በእምነት አኑረን፤
ጸጋህንም አድለን፤
ሰላምህን ስጠን።
ልባችን ወደ አንተ፥
ይናፍቃል በብርቱ፤
ከዓለም እንቅፋት።
፬፡ ከአብ ዘንድ ተሰጥቶሃል፥
በሁሉ ላይ ሥልጣን፤
አንተም በደምህ ዋጀህ፥
የሕዝብህን መዳን።
ሰማይን ታወርሳለህ፤
ጽድቅንም ትሰጣለህ፤
ለሚታመኑብህ።
፭፡ ከአብ የተሰጠህን
ማዳን ፈቃድህ ነው፤
የጠፋውን መንጋህን
ለሕይወት መረጥኸው፤
የሱስ ሆይ ለኔም ራራ፤
እኔንም ካንተ ጋር፥
በመንግሥትህ አኑር።