መዝሙር 154 ጌታችን ሆይ መድኃኒታችን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ጌታችን ሆይ መድኃኒታችን
በጸጋህ ኃይል ወደኛ ና፤
በልጆቸህ መካከል ደግሞ፥
የመንፈስህን ብርሃን አብራ።
፪፡ የሱስ አሁን ወደ ሁላችን
ናና በፍቅርህ አሙቀን፤
ኃጢአታችንን ደምስስልን፤
ወዳንተ ለመሸሽ እርዳን።
፫፡ የኛ ትምክህት ፍጹም ይደምሰስ
ያን ከንቱ ምንጭም አድርቀው፤
የራሳችንም ተስፋ ይጥፋ፥
አምባችን አንተ ብቻ ሁን።
፬፡ ምስጋና ኃይል ውዳሴ ክብር
ለአንተ ብቻ ይገባል፤
በቃልህም እንድንጸና፥
ኃይላችን አንተ ሁንልን።