መዝሙር 15 ሕፃን ተወልዶአል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሕፃን ተወልዶአል
በቤት ልሔም፥ ቤትልሔም።
ደስ ይበልሽ የሩሳሌም፤
ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ።
፪፡ እናቱ ማርያም ንጽሕት
ድንግል ናት፥ ድንግል ናት።
አባቱም አብ በሰማያት፥
ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ።
፫፡ በበረት ውስጥ ተገኘ
ሕፃኑ፥ ሕፃኑ።
መላእክትም ለርሱ ዘመሩ፤
ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ።
፬፡ ሰብአ ሰገልም መጥተው
ሠውለት፥ ሠውለት።
ወርቅና፥ ዕጣን፥ ከርቤም ሰጡት፤
ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ።
፭፡ ሕፃኑ አዳኛችን
ሆኖአል፥ ሆኖአል።
ዕዳችንን ከፍሎልናል፥
ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ።
፮፡ የአምላክ ልጅ በፍቅሩ
መጣልን፥ መጣልን።
በመምጣቱ ደስ ይበለን፥
ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ።
፯፡ አወረደልን ከአብ
ሥምረቱን፥ ሥምረቱን።
በደስታ እናያለን ፊቱን፤
ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ።
፰፡ መላእክት ለጌታ
እንደ ዘመሩ፥ ዘመሩ።
እኛም እንዘምር ለርሱ፥
ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ።
፱፡ ስብሐት ይሁን ለአምላክ
በአርያም፥ በአርያም።
ለኛ ደግሞ ይሁን ሰላም፥
ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ።