መዝሙር 143 በቶሎ ይመለሳል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ በቶሎ ይመለሳል
ሰማያዊ ጌታ።
ሙሽራይቱን ከውርደት፥
ያስነሣል ለክብረት።
የጽድቅ ልብስ ያለብሳታል፥
አክሊልም ይሰጣታል።
የሞቀው የጥንት ፍቅር፥
ይመለስላታል።
፪፡ እንቅልፍ የከበዳት
ሙሽራይቱ ትንቃ።
ከፍርድ ነፃ መሆንዋን፥
ድንቅ ተስፋውን ትስማ።
ለጠፉት ልጆች ሁሉ፥
አምላክ መራራቱን።
በብርሃን መምራቱንም፥
አማኝ ሁሉ ያውራ።
፫፡ እናንተ አሕዛብ ተነሡ
የሱስን እመኑ።
ሕይወት እንድታገኙ፥
በርሱ ብቻ ጽኑ።
በእምነት በርትታችሁ፥
ፍቅራችሁን ግለጡ።
ሕዝብ ወንጌልን ሲቀበል፥
መዳኑን እወቁ።
፬፡ የሱስ መድኃኒታችን
በቅዱሳን መላእክት
ታጅቦ ይመለሳል።
በዚያ በፍርድ ዕለት፥
ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ፥
ለፍርድ ይቀርባሉ።
ጻድቃን ግሩም ብፅዕና፥
በላይ ያገኛሉ።