መዝሙር 10 የሩሳሌም እልል በዪ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሩሳሌም እልል በዪ፤
የጽዮን ልጅም ዘምሪ።
ንጉሥሽ ይመጣልና
በምድር ሁሉ ሊገዛ።
፪፡ ጸጋና ጽድቅን ሊሰጠን
ከአባቱ ተላከልን።
ይሰጣልም ለሰው ሰላም
ከኃጢአት ሁሉ በማዳን።
፫፡ ምሥራች የነገረ መልአክ።
ተልኮልናል ከአምላክ።
በርሱ ያገኘነው ተስፋ
ይሰጠናል ታላቅ ደስታ።
፬፡ ስብሐት ለአምላክ በአርያም
በዓለምም ይሁን ሰላም።
ታላቅ ጸጋ የሰጠንን
በሙሉ ልብ እናመስግን።