Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 93 አምላኬ ሆይ በኃጢአቴ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ አምላኬ ሆይ
በኃጢአቴ
ከባድ ኃዘን ተሰማኝ።
በዚች ዓለም
አንድ ሰው የለም
በጭንቀት የሚረዳኝ።
፪፡ ሩቅም ብሄድ
ረጅም መንገድ
እስከ ዓለም ዳርቻ።
ከየት ላግኝ
ደስታን ሰጥቶ
ከኀዘን የሚፈታኝ?
፫፡ ቸር አምላኬ
ወደ አንተ
እመጣለሁ አሁን።
ተቀበለኝ
አባት ሁነኝ፥
ዘወትር ተገን ሁነኝ።
፬፡ ቸሩ የሱስ
ደካማ ነኝ
ለውጥ ክፉ ጠባዬን።
ትዕግሥት ስጠኝ
አጠንክረኝ
በደስታና በኃዘን።
፭፡ ባንተ ፈቃድ
በቅን መንገድ
እንድሄድ አንተ ምራኝ።
በዚች ዓለም
ብርቱ ሸክም
ልታገሥ ኃይልን ስጠኝ።
፮፡ አብና ወልድ
በባሕርይ አንድ
ከመንፈስ ቅዱሰ ጋራ
ስመኝ አሁን
አዎን አሜን
ጸሎቴን ትሰማለህ።