Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 68 ነፍሴ ሆይ አሁን ደስ ይበልሽ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ነፍሴ ሆይ አሁን ደስ ይበልሽ፤
ኦ ልቤ ሐሴት አድርጊ።
በደሙ የሱስ እንደ ገዛሽ፥
ወንጌል የሚለውን አትርሺ።
አምላክሽም እንደ ወደደሽ፥
ሰው ሆኖ አንችን እንደ ዋጀሽ።
በከንቱም ጸጋውን እንደ ሰጠሸ፥
ይህንን ከቶ አትርሺ።
፪፡ በልቤ ጭንቅ ብቻ ቢሰማኝ፥
እንዳለሁ የሱስ ገዝቶኛል።
ማንኛውም ነገር ቢያስፈራኝ፥
የደሙ ቤዛ በቅቶአል።
ድኃ ብሆን ብከብርም፥
ባዝንም ወይም ደስታ ባገኝም።
በሕይወት ብኖርም ብሞትም፥
የየሱስ ክርስቶስ ገንዘብ ነኝ።
፫፡ በየሱስ ክርስቶስ የሚያምን፥
ከሌላው ሁሉ ታደለ።
በየሱስ ክርስቶስ ደም፥ ሰላምን
ከአምላኩ ተቀበለ።
አምላክ በፍቀር ያየዋል፤
በሕይወት መንገድ ይመራዋል፤
ወደ ብፅዕና ያደርሰዋል፤
ለዚህም የሱስ ገዝቶታል።