Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 40 ካምላክ የራቅነው ኃጥአን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ካምላክ የራቅነው ኃጥአን
ልጆቹ ሊያደርገን
በንጹሕ ደሙ ገዛን
ያ ቅዱስ የአምላክ በግ።
በልብህ ስቃያችንን
ተሸክመህ ዕዳችንን
አዳንኸን ጌታ የሱስ
፪፡ ብርቱ የሚያሰቅቅ
ሥቃይ ሲያስፈራራህ
መንፈስህም ሲጨነቅ
በጻርህ ለኛ ራራህ።
እኛን ለማዳን ስትልም
ሕማምን አልተሰቀቅህም
ተመስገን ጌታ የሱስ።
፫፡ እኛ እንድንባረክ
ባንተ ተጫነ መርገም
ጻርህ እንዴት ይተረክ
መስቀሉን ስትሸከም።
የመቅሠፍት ጽዋ ጠጥተህ
ስለኛ ነፍስህን ሰጠህ
ተመስገን ጌታ የሱስ።
፬፡ የሰማይን ሠራዊት
አንዴ መጥራት ሲቻልህ
የአርያምም ኃይሎች
ሲታዘዙ ለቃልህ
በምድራችን ላይ ታሰርህ
እስከ ሞት ድረስ ታዘዝህ
ተመስገን ጌታ የሱስ
፭፡ ለአንተ ያልራራልህ
አምላክ ግን ለእኔ ራራ
ልቤም ስለ ምሕረትህ
ይሆናል ካንተ ጋራ።
በአንተ እታመናለሁ
ሕይወቴን እሰጥሃለሁ
ተመስገን ጌታ የሱስ።