Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 341 ንቁ ቁሙ ለየሱስ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ንቁ ቁሙ ለየሱስ
እናንት ወታደሩ
የጽድቁን ጥሩር ልበሱ
በእርሱ ተመሩ።
ጠላት ሁሉ እስኪሸነፍ
እርሱ ሊረዳችሁ
ከድልም ወደ ድልም
በርሱ ታምናላችሁ።
፪፡ ንቁ ቁሙ ለየሱስ
ጌታን ተመልከቱ፤
ከላይ ከሰማይ ሲታይ
በደመቀ ፊቱ።
ተነስተን እንገናኝ
በላይ በደመና
በእርሱ ደስ እንዲለን
አምባችን ነውና።
፫፡ ንቁ ቁሙ ለየሱስ
በብርታቱ ቁሙ፤
የሥጋ ክንድ አይችልም
በጨለማ ዓለም።
ስለዚህ ልትድኑ
በፈሰሰው ደሙ
ወንጌልንም ልበሱ
ትእዛዙንም ስሙ።
፬፡ ንቁ ቁሙ ለየሱስ
እናንት ሎላልቱ፤
ዛሬ በዘመቻ ቀን
ለድላችሁ በርቱ።
ለርሱ የሚያሸንፍ
ሊኖር በመንግሥቱ
ተስፋ ተደርጎለታል
በሰማይ ርስቱ።