Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 312 በብፁዓን መኖሪያ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ በብፁዓን መኖሪያ
ነዋሪ ርስት አለን፥
በየሱስ ደም ወደዚያ
ገብተን እንወርሳለን።
መስቀሉን ተሸክመን፥
መከራን ታግሠን፥
አክሊሉን እንድንጭን፥
እንጓዝ ወደ ሰማይ።
፪፤ ከሞትም ባሕር ወዲያ
ሞገዱ ጸጥ ይላል፤
ያሁኑ ችግር በዚያ
አልቆ ይለቀናል።
መስቀሉን . . .።
፫፡ የሱስ ያዘጋጀልን ቤት
ይከፈትልናል፤
ከምድር የተመረጡት
በዚያ ይቆዩናል።
መስቀሉን . . .።
፬፡ ከዓለማዊ ከንቱነት
ልባችን ወደ ላይ
ይናፍቃል ይመኛልም
የሱስን እስክናይ።
መስቀሉን . . .።