Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 311 በአምላክ ዙፋን ፊት የዘፈን ግጥሞች
፩፡ በአምላክ ዙፋን ፊት
ድነው የቆሙት፥
ነጭ ልብስ ለብሰው
ለመድኃኒታቸው
ምስጋና የሚሰጡት፥
እኒያ ማን ናቸው?
እነዚያ ዳኑ በየሱስ
ክርስቶስ ደም፤
ነጹም በበጉ ደም።
፪፡ እኒያ ከታላቅ ጭንቀት መጥተው፥
በበጉ ደም ልብሳቸውን አጥበው፥
የሱስን ተቀብለው፥
የዳኑቱ ናቸው።
እነዚያ ዳኑ . . .።
፫፡ ለዘላለም ድነው ከዚያ ምድር ጻር፥
በበገና በመሰንቆም አውታር፥
በማይሻር አዲስ መዝሙር፥
ደስታን ያሰማሉ።
እነዚያ ዳኑ . . .።