Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 291 ስንት ብፅዕና ታደለ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 291 ስንት ብፅዕና ታደለ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ስንት ብፅዕና ታደለ
የሱስን ያገኘ!
ከርሱ የተዛመደው፥
ልቡ ሰላም አለው።
የእርሱን ቃል ማዳመጥ፥
ከሁሉ ይበልጣል።
ከምሕረቱ እንጥገብ
በእግሩ አጠገብ።
፪፡ ምን አለው ጌጥ ወርቅ ደስታ
የሚበን ትቢያ?
ያመነ በየሱስ ግን፥
አገኘ ድንቅ ሀብትን።
ጤና ትርፍ ወዳጅ ሕይወት
ምንም ቢጠፋበት፥
የሱስ ክርስቶስ ይኖራል፥
ጉዳቱን ይተካል።
፫፡ የሱስ ሆንህልኝ ጋሻ፥
ሰይፍ፥ መዝገብ፥ ትርፍ አምባ።
በሌት ሆነህ ፀሐዬ
የማይክድ ወዳጄ።
በውርጅብኝ ነህ ተገን፥
ማጽንያ በኀዘን።
ኃይል በጭንቀት በድካም፥
በሞት ሕይወት ሰላም።
፬፡ ከኃጢአቴ አጥራኝ፤
ጻድቅም አድርገኝ።
አግባልኝ ቅዱስ ድፍረት፤
አድነኝ ከውድቀት።
ሁን እረኛዬ ዘንጌ፥
አትራቅ ከእኔ።
ከመቃብሬ አንሣኝ
በሰማይ አኑረኝ።

Exit mobile version