Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 25 ዕጹብ የሆነ ጮራ አስገራሚ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ዕጹብ የሆነ ጮራ አስገራሚ
እንዲህ ያለ ሰናይ መዝሙር
መላእክት ሲዘምሩና ሲወድሱት፥
እረኞች በሜዳ ሲሰሙት።
ሰማህ ወይ? ሰማህ ወይ?
መሲሕ እንደ ተወሰለደ ላንተ ሲል?
ብታምንበት ሕይወትን ትወርሳለህ
ስለዚህ በፍጥነት እመነው።
፪፡ በዳዊት ከተማ በቤተልሔም
በበረት ውስጥ የተኛው ሕፃን
ለኛ መድኃኒት ሊሆንልን መጣ
ልባችንን እንክፈትለት።
ሰማህ ወይ . . .።
፫፡ የሕፃኑን መወለድ እረኞቹ
በረኝነት ሳሉ ሲሰሙ
ለማየትና እርሱን ለማመስገን
በፍጥነት ወደ በረት ሄዱ።
ሰማህ ወይ . . .።
፬፡ ለተወለደው ሕፃን ጠቢባኑ
እጅ መንሻ ይዘው ሰገዱለት
አንተስ ምን ልትሰጠው አስበሃል
አንተንም ይጠባበቅሃል።
ሰማህ ወይ . . .።