Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 224 ይመራኛል፥ ይመራኛል የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ይመራኛል፥ ይመራኛል፥
እንዴት ያለ መጽናናት ነው!
በሄድሁበት፥ ባለሁበት፥
ይጠብቀኛል በሕይወት።
ይመራኛል፥ ይመራኛል፥
ጌታ የሱስ ይመራኛል፥
በመንፈሱ ከተመራሁ፥
ተከታዩ እሆናለሁ።
፪፡ ጌታዬ ሆይ፥ እኔን እርዳኝ፤
ከማጕረምረምም ጠብቀኝ።
በፈተና ኃይል እንዳገኝ፥
አምላኬ ሆይ እኔን እርዳኝ።
ይመራኛል . . .።
፫፡ በዚህ ዓለም ስትመራኝ፥
በጸጋህ ካገኘሁ ሁሉን፥
አልፈራም የሞትን ጥላ፥
አንተ ካለህ ከኔ ጋራ።
ይመራኛል . . .።