Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 220 ክብር ላንት የሱስ ሆይ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ክብር ላንት የሱስ ሆይ
ክብር ላንተ፤
አድምፀኝ በጸሎት
ስንበረከክ።
ይህ ነው የኔ ምኞት
ክብር ላንተ የሱስ
ክብር ላንተ፥ ክብር ላንተ።
፪፡ ፊት ያለምን ደስታ
እመኝ ንበር፤
አሁን ግን ምኞቴን
ጸጋህን ስጠኝ።
ይህ ነው የኔ ተስፋ
ክብር . . .።
፫፡ ኀዘን ወይም ትካዜ
ቢሰማኝም፥
በደስታ በትዕግሥት
ልቀበለው።
ይህ ነው የኔ ምኞት
ክብር . . .።
፬፡ ሕዋሳቴ ሁሉ
ያመስግኑህ፤
ይህ ነው ፍላጎቴ
በልቤ ውስጥ
የኔ ተስፋ ደግሞ።
ክብር . . .።