Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 219 ከዘላለም የወጣ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ከዘላለም የወጣ
ያ መለኮታዊ ፀሐይ
በዚህ ቀን ለኛ ይብራ
ያሙቀን ደማቅ ብርሃኑ
ጨለማን ያርቅልን
ብርሃን እንዲበራልን።
፪፡ በሕያው መንፈስ ቅዱስ
ደረቁን ሕሊና አርስ።
በጸጋህ አነቃቃን
ለወንጌልህ ሥራ አትጋን።
በመንፈስ አጠንክረን
ፍሬያም እርሻ አድርገን።
፫፡ ባባትነትህ ፍቅር
ልንኖር ለአንተ ክብር
ቅን ልብ በእኛ ፍጠር
ያንተን መንግሥት ለማስፋፋት።
ስጠን ኃይልና ድፍረት
አውርድልን በረከት።
፬፡ የፍርድ ቀን ሲደርስብን
ጸጋና ምሕረትን ስጠን።
የክብርህ ተካፋዮች
እንድንሆን ደግሞ አብቃን
አድለነ በጸጋ
የዘላለም ብፅዕና።
፭፡ አንተ የሰማይ ብርሃን
ከዓለም ጨለማ ጠብቀን
አርቅልን ስንፍናን።
ብፅዕና በሚገኝባት
ደስታ በሞላባት
አኑረን በሰማይ ቤት።