Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 200 በክርስቶስ ጸጋ እንድንድን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ በክርስቶስ ጸጋ እንድንድን
ከዘለዓለም ተመረጥን።
አምላክ በጸጋው ይሰጠናል
የኃጢአት ስርየት።
በምድርና በሰማያት
ለየሱስ ክርስቶስ ክብር ይሁን።
ኃጢአታችን ተሰረየ፥
አሜን ሃሌ ሉያ።
፪፡ ዓለም ተገዛ በየሱስ ደም፤
እርሱ አዳነን ሃሌ ሉያ።
በሙሴ ሕግ ለታሠሩትም
ነፃነት ሰጥቶአል።
በምድር . . .።
፫፡ ኦ ክርስቶስ ሆይ ስለ ገዛኸኝ፥
አንተን ላመሰግን ራስህ እርዳኝ።
በአንተ ቅዱስ ጻድቅም ነኝ።
በራሴ ምስኪን ነኝ።
በምድር . . .።