Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 182 የሕይወትን ምንጭ ስመለከት የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሕይወትን ምንጭ ስመለከት፣
ለኔ የፈሰሰውን፥
የመንፈስን ጥሪ ሰማሁ፥
የሚለውን ነፃህ ወይ?
ላመስግነው፡ ላመስግነው፥
ለኔ የሞተውን በግ፥
ክብር ስጡት ሰዎች ሁሉ
በደሙ አንጽቶናልና።
፪፡ የጌታ ስም ብሩክ ይሁን
እኔን የተቀበለኝ፥
በደሌን ይቅር ብሎኛል፥
ከኃጢአት አንጽቶኛል።
ላመስግነው፥ . . .።
፫፡ ክብር ፡ ክብር ለአብ ይሁን
ክብር ደግሞ ለልጁ፡
ክብር ለመንፈስ ቅዱስም
ክብር ለመለኮቱ።
ላመስግነው፥ . . .።