Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 165 ያምላካችን ታናሽ ጭፍራ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ያምላካችን ታናሽ ጭፍራ፥
ቤቱ ነው በጽኑ ስፍራ።
አምላክ ይሆነዋል ጋሻ፥
የለም የሚያስፈራራው።
፪፡ ልጆቹ ባምላክ ተራራ፥
ይኖራሉ ከርሱ ጋራ።
እርሱም ልጆቹን ይጠራል፥
ሰርክ ሲጠብቅም ይኖራል።
፫፡ ደስታ ሆነ ወይም ጭንቀት፥
ልጁን ከርሱ እጅ አይነጥቅም።
ያ ወዳጅ በጽኑ እጁ
ጋሻ መክቶአል ለልጁ።
፬፡ የራስ ጸጉራችን ሁሉ፥
ባምላክ ዓይን ይቆጠራሉ።
አምላክም ይመግበናል
በርሱም ፍቅር ደስ ይለናል።
፭፡ ቢሰጠንም፥ ቢነሣንም
አባትነቱን አይረሳም።
ሐሳቡም ለጥቅማችን
ነው በመላ ዘመናችን።
፮፡ ደስ ይበልህ ታናሽ መንጋ፤
አምላክህን አትዘንጋ።
ጠላቶችም ቢነሡብህ
በእርሱ ኃይል ይጠፋሉ።