Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 131 ከአምላክ ጋር በመገናኘት የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ከአምላክ ጋር በመገናኘት
ሰው ሆይ ታገኛለህ ሕይወት።
ስትለይም ከዓለም ሁከት
ይሰጥሃል ሰላም ዕረፍት።
ልብህ መጽናናት ያገኛል
ባምላክ ምሕረት ይደሰታል።
፪፡ ምስጉን እርሱ በቃል በሥራ
በአምላክ ሕግ የሚመራ፤
በቅድስና ወደ ሰማይ
በሃይማኖት ዓይኑ የሚያይ
ይቀምሣል በምድር እንኳ፥
ያምላክን መንግሥት ብፅዕና።
፫፡ ሰዎች በከንቱ ይጥራሉ
በከንቱም ይቃትታሉ
እናንተ ብፅዕና የምትሹ
ያምላክን ምሕረት አትርሱ።
ታላቅ ፍቅሩ የሠራውን
ተመለክቱ በእምነት ዓይን።
፬፡ ነዋሪ ሀብቱ ለሰው ሁሉ
የዘለዓለም ሕይወት ነው።
በዚህ ነው ነፍስ የምትደሰት
ታላቅ ረብ የሚሆንላት።
ያምላክን ወንጌል መርምሩ
ሰማያዊ ሀብትን እሹ።
፭፡ የሰማይ በር ተከፍቶልኛል
ቅዱስ አምላክ ይጠራኛል።
በማይናወጥ ፍቅሩ ሊያኖረኝ
ምሥጢሩንም ገለጠልኝ።
የማዳኑን ጸጋ ሰጠኝ
በሥምረቱ አሳደረኝ።
፮፡ በእምነት ከኃጢአት ስለ ዳንሁ
ጌታን አመሰግናለሁ።
መጠራጠር ሲነሣብኝም
ካምላክ ፍቅር አልለይም።
ጌታዬ ይጠብቀኛል
በመንፈሱም ይመራኛል።